6. ሙስሊሞች መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ አይጠበቅባቸውም
በርካታ ሙስሊሞች፣ ቁርአን ከእርሱ በፊት የመጡትን ቅዱሳት መጻሕፍት የተካና ለሰዉ ልጆች የተሰጠ የመጨረሻ መገለጥ ነው በማለት መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ አስፈላጊያችን አይደለም በማለት ይሞግታሉ፡፡ ከዚህ በተቃራኒው፣ ሙስሊሞች በቁርአን ብቻ ሳይሆን ለነቢያት በወረዱት (በተገለጡት) ቅዱሳት መጻሕፍት ጭምር እንዲያምኑ ቁርአኑ ራሱ ያዛቸዋል፡-
Ø በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርአን) ወደ ኢብራሂምም [አብርሃምም] ወደ ኢስማዒልና [እስማኤልና] ወደ ኢስሐቅም [ይስሃቅ] ወደ ያዕቁብና [ያዕቆብና] ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ [ሙሴና ኢየሱስ] በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸዉ በተሰጡት ከነርሱ በአንዱም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን% እኛም ለርሱ (ለአላህ) ታዛዦች ነን በሉ፡፡
ሱረቱ አል-በቀራህ (2)፡136
Say ye: “We believe in God, and the revelation given to us, and to Abraham, Isma’il, Isaac, Jacob, and the Tribes, and that given to Moses and Jesus, and that given to (all) the prophets from their Lord; We make no difference between one and another of them.
Ø መልክተኛዉ ከጌታዉ ወደርሱ በተወረደው አመነ፤ ምእምኖቹም (እንደዚሁ)% ሁሉም በአላህ በመላእክቱም፣ በመጻሕፍቱም [ብዙ ቁጥር]፣ በመልክተኞቹም፣ ከመልክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም፣ (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ፣ ሰማን፣ ታዘዝንም፣ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን) መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው አሉም፡፡
ሱረቱ አል-በቀራህ (2)፡285
The Apostle believeth in what hath been revealed to him from his Lord, as do the men of faith. Each one (of them) believeth in God, His angels, His books, and His apostles.
Ø እላንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልክተኛው፣ በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደዉ መጽሐፍ፣ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ፣ በአላህና በመላእክቱም በመጽሐፎቹም፣ በመልክተኞቹም በመጨረሻዉም ቀን የካደ ሰው (ከዉነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡
ሱረቱ አል-ኒሳእ (4)፡136
O ye who believe! Believe in God, and His apostle, and the scripture which He sent to His apostle, and the scripture which He sent to those before (him). Any who denieth God, His angels, His Books, His apostles, and the Day of Judgment hath gone far, far astray.
በብዙ ቁጥር የተጠቀሰዉን "መጻሕፍቶቹን" የሚለዉን ቃል ልብ ይበሉ፡፡ ይህም ቁርአኑንን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ሚጨምር ያመለክታል፡፡ "…ወደ እኛ በተወረደው [በወረደው] (በቁርአን) ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው፣ በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንሆን አመንን፣…" ይህ ጥቅስ፣ ሙስሊሞች የተወሰኑ ቅዱሳት መጻሕፍት ከሌሎቹ የተሻሉ እንደሆኑ አድርገው እንዳይቆጥሩ በግልጽ የሚያሳስብ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል መርሆዎች ለሁሉም ሕዝብ፣ በማንኛውም ጊዜ ያው ናቸው፣ አይለወጡምም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለሆነ ነቢይ የተሰጠ አንድ ቅዱስ መጽሐፍ ሳይሆን እንደ፣ የሙሴ መጻሕፍት (ቶራ)፣ የዳዊት መዝሙሮች (ዛቡር)፣ የኢየሱስ ትምህርቶች (ኢንጅል) እና የነቢያት መጻሕፍቶች (ሱሁፍ-ኡን ናቢዪን) በአንድ ላይ ያካተተ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥርቅም መሆኑን ሙስሊሞች ሊረዱ ይገባል፡፡ እርግጥ ነው አንድ ሰው በቅዱሳት መጻሕፍት ለማመን ማንበብ ብቻ ሳይሆን ሊያጠናቸው ይገባል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ቁርአን ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
Ø እነዚያ መጽሐፉን የሰጠናቸው ተገቢ ንባቡን ያነቡታል [They study it as it should be studied]፣ እነዚያ በርሱ ያምናሉ፣ በርሱም የሚክዱ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው፡፡
ሱረቱ አል-በቀራህ (2)፡121
Those to whom We have sent the Book study it as it should be studied; they are the ones that believe therein. Those who reject faith therein,-the loss is their own.
እስልምና ስለ እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ሌላ ጠቃሚ መረጃ ይሰጠናል፣ ይህም እነዚህ መጻሕፍት የሰውን ዘር ለመረዳት ከአላህ ዘንድ የተላኩ ምልክቶች መሆናቸውን፡፡ በዚህ ምክንያት እያንዳንዱ የቅዱስ መጽሐፍ ጥቅስ አያት (ምልክት) በመባል ይታወቃል፡፡ እነዚህ ምልክቶች በቸልታ እንዲታዩ ቁርአኑ ይፈቅድም፤ ስው ሁሉ እንዲቀበላቸው እንጂ፡፡ ለእነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ (አንዱን ከአንዱ ሳይለይ) ምልክትነት ጀርባቸውን ለሚሰጡ ሰዎች ቁርአኑ የሚያስተላልፈውን መራር ማስጠንቀቂያ ከዚህ በታች ይመልከቱ፡-
Ø እነዚያን በተአምራታችን የካዱትን በእርግጥ እሳትን እናገባቸዋለን፣ ስቃይን እንዲቀምሱ ቆዳዎቻቸዉ በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለዉጥላቸዋለን፣ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነዉና፡፡
ሱረቱ አል-ኒሳእ (4)፡56
Those who reject Our signs, We shall soon cast into the Fire.
Ø እነዚያም የካዱና በተአምራቶቻችን ያስተባበሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸዉ፡፡
ሱረቱ አል-ማኢዳህ (5)፡10
Those who reject faith and deny Our signs will be companions of Hell-fire.
No comments:
Post a Comment